OCC የ2024 የኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት አገኘ ።
2024-11-18 11:09:55
በለፈው ወር በአፍሪካ ደረጃ የምሰጠውን ሽልማት በ “African Union Development Agency and Japan International corporation agency (AUDA & JICA)” ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን ሽልማት የወሰደው OCC ዛሬ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፍ 3ኛ በመሆን የኢትዮጵያ ካይዘን ድርጅትን ሽልማት ማግኘት ችሏል። ሽልማቱ በአፍሪካ ሀገራት ካይዘንን ተግባራዊ ያደረጉ ድርጅቶችን አወዳድሮ በደረጃ በማስቀመጥ የሚሰጥ ነው። የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (OCC) ካይዘንን ያለማቋረጥ በመተግበር ተጨባጭ ውጤት እና መሰረታዊ ለውጦችን በማሳየት ለሽልማቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲወዳደር በ“Ethiopian Kaizen Excellence center(KEC) ተመርጠው ነው። ኮርፖሬሽኑ ሽልማቱን ለመቀበል ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለሙያዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲገመገም የቆየ ስሆን በተለያዩ አካላት በተደረገው ግምገማ በፊንፊኔ ጋራጅ ማዕከል በካይዘን አተገባበር ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ከተለያዩ አህጉራት በተወጣጡ የሽልማት ኮሚቴዎች ተቀባይነት አግኝቶ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዘርፍ የ3ኛ ደረጃ የ2024 ሽልማት ሲያገኝ የገላን የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በቡድን ሦስተኛ በመሆን የሜዳልያ ሽልማት፣የአለምገና ጋራጅ ማዕከልም ደግሞ የእውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ።