no image no second image no Third image no forth image no Fifth image

የላይኛው ጉደር መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ 10 ሺህ በላይ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

2022-10-21 16:11:54

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሸዋ ዞን በባለቤትነት የሚያስገነባው የላይኛው ጉደር መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ሲጠናቀቅ 10 ሺህ በላይ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ የላይኛው ጉደር መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግድብና ተያያዥ ስራዎች የሚገነባው በፋጦ ወንዝ ላይ በቶኬ ኩታዬና በድሬ ኢንጭኒ ወረዳዎች እንዲሁም የመስኖና ዲሬይኔጅ መሰረተ ልማት በቶኬ ኩታዬና አምቦ ዙሪያ ወረዳዎች ውስጥ ነው፡፡ የግድብና የመስኖ መሰረተ ልማቱ ግንባታ በዋናነት የሚያካትተው የግድብ ግንባታ ፣ 23 ኪሎ ሜትር ጂ.አር.ፕ. ቧንባ ፣ 150 ኪሎ ሜትር ዩ.ፕ.ቭ.ሲ.ቧንባ፣ 4.7 ኪሎ ሜትር ዋና ቦይ ቧንባ ፣ 4.5 ኪሎ ሜትር ዋና ቦይ የመጀመሪያ ቧንባ ፣13 ኪሎ ሜትር ዋና ቦይ ሁለተኛ ቧንባ ፣ 4926 ሄክታር የመስኖ መሰረተ ልማት ናቸው ፡፡ የግድብና ተያያዥ ስራዎች ግንባታ(ሎት -1) በ2014 በጀት ዓመት መጨረሻ ከነበረበት 34.29% በ2015 በጀት ዓመት መጨረሻ ወደ 69.29% እንዲሁም የመስኖ መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች(ሎት-2) በ2014 በጀት ዓመት ከነበረበት 7.59% በ2015 በጀት ዓመት መጨረሻ ወደ 58.34% ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡ የላይኛው ጉደር ግድብ ከፍታው 40.1 ሜትር፣ ርዝመቱ 277 ሜትር ያለው ሲሆን ግደቡ 56 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ይይዛል፡፡ፕሮጀክቱ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ 4926 ሄ/ር ያለማል ፡፡ ፕሮጀክቱ በቶኬ ኩታዬና አምቦ ዙሪያ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሚ አርሶአደሮች በዓመት ውስጥ የተለያዩ ሰብሎችንና ፓፓያ ፣ሙዝ ፣ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉትን ከ 2—3 ጊዜ ማምረት ያስችላቸዋል ፡፡ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የግድብ ግንባታና ተያያዥ ስራዎችን የሚሰራ ሲሆን ኦሮሚያ ኮንስትክሽን ኮርፖሬሽን የመስኖ አውታርና ተያያዥ ስራዎችን ይሰራል ፡፡ የማማከሩን ስራ የሚሰራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቭዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በ2014 በጀት ዓመት ወንድ 497 ሴት 190 ድምር 687 ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞች የስራ እድል ፈጥሮዋል ፡፡ በተጨማሪም 2 ስራ ተቌራጮችና አንድ አማካሪ ድርጅቶች የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጭ 3.4 ቢሊዮን ብር ይሆናል ፡፡ የፕሮጀክቱ ተግዳሮት የመስኖ ቱቦ ግዥ መዘግየትና ማህበራዊ ችግሮች ሲሆኑ የሚመለከታቸው የሥራ ሃላፊዎች በየደረጃው ካለው መስተዳድር አካላት ጋር በመወያየት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡ ፕሮጀክቱ በመስከረም 2012 ተጀምሮ በሰኔ 2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ ታቅዶዋል ፡፡ (ከመስኖ እና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር) ... እናም ሁሉም የድርሻዉን ለመወጣት ይዘጋጅ ለማለት ነዉ